የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ከየትኛውም ዜጋ በላይ ዋስትና እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ። በአገራቸው ጉዳይ ላይ በተለይም በዕርቅ ዙሪያ በርካታ ጽሁፎችን ሲያቀርቡና ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በኃላፊነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከአገራቸው ውጪም በኬንያ፣ በሞዛምቢክ፣ በስዊትዘርላንድና በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በከፍተና ኃላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በተለይም በዎርልድ ቪዥን፣ በተባበሩት መንግሥታ፣ [...]
↧