ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም 50ኛ ዓመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የመጀመርያ ዙር ተመራቂ ናቸው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አሜሪካ ከሚገኘው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ያገኙ ሲሆን፣ የፒኤችዲ ዲግሪም ያገኙት እዚያው አሜሪካ ነው፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ በቀይ ሽብር ምክንያት ከአገር ከመሰደዳቸው በፊት በሕግ አማካሪነትና በጠበቃነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በአሜሪካ ከ20 ዓመታት በላይ በማስተማር ሥራ ላይ [...]
↧