ሰማያዊ፡- የሰማያዊ ፓርቲ ምሰሶ የሚባሉ ዋና ዋና የሚያራምዳቸው ፖለቲካዊ አቋሞች ምንድናቸው? ኢ/ር፡ ይልቃል፡- ፖለቲካ በየጊዜው እንደሁኔታው የሚለወጥ& የሚሻሻልና የሚያድግ ቢሆንም! ሰማያዊ ፓርቲ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታሪክና ካሉብን ችግሮች በመነሳት ዋና ዋና የምንላቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡- አንደኛ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ የተለያየ ልማድ& ባህል& ቋንቋ እና እምነት ያላቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ የወል ስነ-ልቦና አዳብረው [...]
↧