“ጥቁሩ ሰው” ይሉታል። ኢትዮጵያዊያን ለሚያሽከረከራት አስፈሪ ፈተና መፍትሄው ሰብአዊነትን ማስቀደም ብቻ ነው የሚል የጸና እምነት አለው። “ከጎሳ በፊት ሰብዓዊነት” በሚል መሪ ዓላማ ከሚመስሉት ጋር በመሆን ድርጅት አቋቁሞ መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባከናወናቸው ሥራዎች ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰማው ያምናል። ኢትዮጵያዊያን ችግር ደርሶባቸዋል በሚባልበት ሁሉ ቀድሞ ደራሽ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። በዚህና በሰብዓዊ መብት ጉዳይ በሰራቸው ስራዎቹ ቁጥራቸው ቀላል [...]
↧